ሀገር አቀፍ የፍትህ አካላት የምክክር መድረክ በባህር ዳር ከተማ ተካሄደ፡፡

በምክክር መድረክ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ክብር አቶ አያሌ ጉበዜ እንደገለፁት ሀገሪቱን ከድህነትና ኋላቀርነት ለማላቀቅ በሚደረገው ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴ የፍትህ አካላት ከመቸውም ጊዜ የበለጠ ርብርብ በማድረግ የተቀላጠፈና ውጤታማ የሆነ ፍትህ ለህብረተሰቡ መስጠት ይገባል ብለዋል፡፡

የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማሪያም በበኩላቸው ከአጐራባች ክልሎች ጋር የነበሩ አንዳንድ ግጭቶችና አለመግባባቶች እየቀነሱ የመጡ ቢሆንም ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡ የምዕተ ዓመቱን የፍትህ ዕቅድ ለማሳካት በዋናነት የፍትህና የሠላም ሠራዊት መገንባት ወሳኝ በመሆኑ ህብረተሰቡን ከፍትህና ከሠላም ሠራዊት ጋር በማያያዝ ውጤት ተኮር ስርዓቱን በይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ሲሉ ጨምረው አሳስበዋል፡፡

የሀገር አቀፍ የፍትህ አካላት የምክክር መድረክ ከመስከረም 21-23/2005 ዓ/ም የተካሄደ ሲሆን የዚህ መድረክ ዓላማ በዋናነት ለምዕተ ዓመቱ የፍትህ ዕቅድ ለማሳካት የፍትህ አካላቱን የተግባር አፈፃፁም በጋራ በመወያየት፣ በመገምገም እንዲሁም የቀጣይ 2005 ዓ/ም የትኩረት አቅጣጫዎች ለማስቀመጥ ነው፡፡ በምክክር መድረክ ቆይታ የ2004 በጀት ዓመት የፌዴራል እና የተመረጡ የክልል የፍትህ አካላት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖረት እንዲሁም የ2005 ዓ/ም በጀት ዓመት የፌዴራል ጉዳዮች ዕቅድ ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡ የ2004 በጀት ዓመት የፍትህ አካላት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት፣ በሰው ኃይል ግንባታ፣ የውጤታማነት፣ የቅልጥፍና የተደራሽነት፣ የግልፀኝነትና ተጠያቂነት እንዲሁም ህብረተሰቡን ከማሳተፍ አኳያ ትኩረት ተሰጥቶ ውይይት የተደረገባቸው ነጥቦች ናቸው፡፡ በረፖርቱ እንደተገለፀው በፍትህ አካላት በሰው ኃይል ግንባታ ዙሪያ ከአጭር እስከ ረዥም ጊዜ ስልጠና የተሰጠ ቢሆንም በቁጥር ደረጃ ግን ውስን መሆኑ ተገልጾል፡፡ የውጤታማነት፣ቅልጥፍናና ተደራሽነት ጋር ተያይዞ የክልሎች አፈፃፀም ከዓመት ዓመት መሻሻል መታየቱ እንዲሁም ውጤታማ እየሆኑ መምጣታቸው ተገልጾል፡፡ በህብረተሰቡ እና በመንግስት ከፍተኛ ስጋት የሆነው ከሽብረተኛነት ጋር ተያይዞ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ተከታትሎ ተመጣጣኝ የፍርድ ውሳኔ ከማሰጠት አኳያ የተሰራው ስራ አበረታች ነው ተብሏል፡፡

የፍትህና የሠላም ሠራዊት ግንባታ፣ የኪራይ ሰብሳቢነትን ከመታገል አኳያ ክፍተት መኖሩ፣ የንቃተ ህግ ትምህርት በስፋት ቢሰጥም ህብረተሰቡን ግንዛቤ ከማስጨበጥ አኳያ ጥራቱን የጠበቀ ያለመሆኑ፣ በተከሳሽና ምስክር በየጊዜው ባለመቅረብ ምክንያት የሚዘጉ መዝገባት ቁጥር መበራከት፣ የሀሰተኛ ምስክሮች መበራከት በፍትህ አሰጣጡ ላይ ክፈተት መፍጠራቸው፣ በአንዳንድ ክልሎች የኮሚኒቲንግ ፖሊስንግ አስፍቶ አለመሄድ እና የህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ማቆም ያለመቻሉ በመከክር መድረኩ ወቅት የተጠቀሱ ዋና ዋና እጥረቶች ናቸው፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልል የቀረበው ሪፖርትና የተከናወኑት ተግባራት አስተማሪ በመሆናቸው ሌሎች ክልሎች ከአማራ ክልል የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎችን እና ልምዶችን በመውሰድ ሊተገብሩት እንደሚገባ ተገልጿል፡፡ ሪፖርቱን መነሻ በማድረግ በአማራ ክልል የሚገኙ በተመረጡ ምርጥ ተሞክሮዎች ላይ የመሰክ ጉብኝት የተካሄዶባቸዋል፡፡ በባህር ዳር ከተማ፣ በወረታ ከተማ፣ በሊቦ ከምከም ወረዳ በሸሆች ቀበሌ የኮሙኒቲግ ፖሊሲንግ ምርጥ ተሞክዎችን ከህብረተሰቡ ጋር ሁሉም ተሳታፊዎች ተገኝተው ጎብኝተዋል፡፡

ከቀበሌው ማህበረሰብ ጋርም ተወያይተዋል፡

በመጨረሻም ተሳታፊዎች በአስተዳደርና ፀጥተ ጉዳዮች ቢሮ አዘጋጅነት በክልሉ የሚገኙ የመስህብ ቦታዎችን እና በክልሉ እየተዘገቡ ያሉ መሠረተ ልማቶችን ተዘዋዋረው ጐብኝተዋል፡፡

የቢሮውን የ2005 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ በሚዛናዊነት የውጤት ተኮር አስተቃቀድ ስርዓት በማቀድ የዕቅድ ርክክብ ተደረገ፡፡

የአብክመ አስተዳዳርና ፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ የ2005 የበጀት ዓመት ዕቅድ በሚዛናዊ የውጤት ተኮር አስተቃቀድ ስርዓት በማዕቅድ ከተቋሙ አመራሮችና ፈፃሚ ሰራተኞች ጋር አስፈላጊውን የዕቅድ ኦሬንቴሽን ከተሰጠ በኋላ ወደ ተግባር ተገብቷል፡፡

የ5 ዓመቱ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ፣ የBSC ዕቅድ እና የ2004 ዓ/ም ዕቅድ አፈፃፀም መነሻ በማድረግ በ2005 በጀት ዓመት ቢሮው ትኩረት ሰጥቶ የሚያከናውናቸውን ተግባራት ነቅሶ በማውጣት ዕቅዱ እንዲዘጋጅ ተደርጓል፡፡ የታቀደው ዕቅድ ለእያንዳንዱ የስራ ሂደት በመከፋፈል በ01/02/2005 ዓ.ም በቢሮው ኃላፊ በአቶ ደሴ አሰሜ አማካኝነት ለስራ ሂደት መሪዎች የዕቅድ ርክክብ ተደርጓል፡፡

የማኔጅመንት አባላት በዕቅዱ ላይ ሲወያዩ የሂደት መሪዎች ከኃላፊው ዕቅድ ሲረካከቡ

የዚህ ዕቅድ ካስኬድ መደረጉ ዋና አላማ በቢሮው የሠላም ሠራዊት ግንባታን በማጠናከር ወደ ስራ ለማስገባት፣ በተቋሙ የግልፀኝነትና የተጠያቂነት ስርዓት ለመዘርጋት፣ በሠራተኛው ዘንድ የስራ የውድድር መንፈስ ለመፍጠር፣ሠራተኛው ተግባራትን በኘሮግራም እንዲመራ ለማስቻል ፣ ጠንካራ ሠራተኞችን ለማበረታታና ደካምችንም ወደ ተግባር ለማስገባት መሆኑን አቶ ደሴ አሰሜ ተናግረዋል፡፡

ለሂደቶች የተሰጠው ዕቅድ በየሂደቱ ለሚገኙ ፈፃሚ ባለሙያዎች ርክክብ ተደረጋል፡፡በቀጣይም ዕቅድን ካስኬድ በማድረግ ለዞንና ለወረዳዎች በተመሳሳይ መልኩ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡

የሂደት መሪዎች ከፈፃሚዎች ጋር ዕቅድ ሲረካከቡ

የሠላም ሠራዊት ግንባታን ትኩረት ሰጥተን በመንቀሳቀስ ቢሮው ያቀዳቸውን ተግባራት ሳይንጠባጠቡ በማከናወን የጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ራዕይ ለማሳካት ከመቸውም ጊዜ የበለጠ መትጋት ይኖርብናል ሲሉ አቶ ደሴ ጨምረው አሳስበዋል፡፡

 

 
Selected photos from gallery
  • Photo Title 1
  • Photo Title 2
  • Photo Title 3
  • Photo Title 4
  • Photo Title 5